Copyright 2024 - Marathon Motor Engineering Ethiopia

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ

ሃገር በቀል የሆነው ኩባንያችን ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭና ዘመናዊ የሆኑትን የተለያዩ በጋዝና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሃንዳይ ተሽከርካሪዎች ገጣጣሚና አከፋፋይ እንዲሁም ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስና በከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በድህረ ሽያጭ ዘርፍም በተለያዩ ቅርንጫፎቹ ደረጃውን የጠበቀ የጥገና አገልግሎት እንዲሁም ኦሪጅናል መለዋወጫዎችን በማቅረብ ለደንበኞቹ የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ ኩባንያ ሲሆን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሥራ መስኮች ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

1ኛ.  የስራ መደብ ፡ ሲኒየር የመለዋወጫ ሽያጭ ባለሙያ ( Senior counter sales person) 

 ብዛት፡  አንድ             

 ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ/ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ 3 እና ከዛ  በላይ ያለው/ያላት፡፡

የሥራ ልምድ፡  5 ዓመትና ከዛ በላይ ከፍተኛ የሽያጭ ባለሙያ ( Senior counter sales person) ሆኖ ያገለገለ/ያገለገለች

2ኛ.  የስራ መደብ ፡  የመለዋወጫ ሽያጭ ባለሙያ(counter sales person)   

 ብዛት፡  አንድ             

 ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ/ ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ 3 እና ከዛ  በላይ ያለው/ያላት፡፡

የሥራ ልምድ፡  3 ዓመትና ከዛ በላይ  የሽያጭ ባለሙያ (counter sales person) ሆኖ ያገለገለ/ያገለገለች

3ኛ.  የስራ መደብ ፡  የመረጃ ማዕከል ባለሙያ (Information Desk officer)   

 ብዛት፡  አንድ             

 ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ/ ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ 3 እና ከዛ  በላይ ያለው/ያላት፡፡

የሥራ ልምድ፡  3 ዓመትና ከዛ በላይ የመረጃ ማዕከል ባለሙያ (Information Desk officer) ሆኖ ያገለገለ/ያገለገለች

4ኛ.  የስራ መደብ ፡  ሞተረኛ (Motorist)    

 ብዛት፡  አንድ             

 ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀና የሞተር ብስክሌት መንጃ ፍቃድ ያለው/ያላት

የሥራ ልምድ፡  3 ዓመትና ከዛ በላይ በሞተረኛነት ያገለገለ/ያገለገለች

ቅጥር፡ በቋሚነት

ደመወዝ ፡ በስምምነት

ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን የምታሟሉና ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የሥራ ልምድና የትምህርት ማስረጃችሁን ኦሪጂናልና ኮፒውን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 6(ስድስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ሳሪስ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት የሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ  ምድር ቤት በአካል በመገኘት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 251-114-7092-71 ይደውሉ፡፡

ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ሳሪስ ማራቶን ህንጻ ምድር ቤት

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጽያ

የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን ጥር 20/2014ዓ.ም

Comments powered by CComment

f t m

Contact Us

Head Quarter: Saris

Phone: +251 114 707 322

Fax: +251 114 709 940

whoIsOnline

We have 121 guests and no members online